Announcement በኮሌጁ ተቋማዊ ሞደል የሙያ ብቃት ምዘና ተጀመረ!!

በኮሌጁ ተቋማዊ ሞደል የሙያ ብቃት ምዘና ተጀመረ!!

22nd July, 2025

ሐሙስ:- ሐምሌ 3 ቀን 2017 ዓ.ም 2017 ዓ.ም
በኮሌጁ ተቋማዊ ሞደል የሙያ ብቃት ምዘና ተጀመረ!!
በኮሌጁ ለ2017 ዓ.ም ተመራቂ ሰልጣኞች ተቋማዊ ሞደል የሙያ ብቃት ምዘና በዛሬው ዕለት መሰጠት ተጀመረ::
በጀነራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 ዓ.ም 1625 ተመራቂ ሰልጣኞች ያሉ ሲሆን ዛሬ የተጀመረውን ተቋማዊ ሞዴል በማጠናቀቅ የሙያ ብቃት ምዘና ማዕከል ለሚሰጠው የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ይዘጋጃሉ ተብሏል።

በኮሌጁ እየተሰጠ ያለው ምዘና የፅንሰ ሀሳብ እና የተግባር ሲሆን የፅንሰ ሐሳቡ ምዘና online እየተሰጠ ይገኛል።
የተቋማዊ ምዘናው ዋና ዓላማው ለሀገር አቀፉ የብቃት ምዘና ከመቅረባቸው በፊት ያላቸውን እውቀትና ክህሎት ለመፈተሽ እንዲሁም ያለባቸውን ክፍተት ለመሙላት እንደሆነ በኮሌጁ የስልጠና እና አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ዲን ከሆኑት አቶ ጄበሳ ሙላቱ ሰምተናል።
የ2017 ተመራቂ ሰልጣኞች ነሐሴ 25 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚመረቁ የሚጠበቅ ሲሆን ሰልጣኞች መመረቅ የሚችሉት የሙያ ብቃታቸውን ሲያረጋግጡ ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።
"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

.

Copyright © All rights reserved.

Created with