Online Admission የCOC ምዘና ውጤትን ለማሻሻል የዊንጌት ክላስተር ኮሌጆችና የትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣኑ በቅንጅት ሊሰሩ ተስማሙ

የCOC ምዘና ውጤትን ለማሻሻል የዊንጌት ክላስተር ኮሌጆችና የትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣኑ በቅንጅት ሊሰሩ ተስማሙ

15th July, 2026

ሰኞ:- ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም
 
የCOC ምዘና ውጤትን ለማሻሻል የዊንጌት ክላስተር ኮሌጆችና የትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣኑ በቅንጅት ሊሰሩ ተስማሙ፡፡
 
የጀነራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅን ጨምሮ በዊንጌት ክላስተር ስር የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች እና የትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች የብሔራዊ የሙያ ብቃት ምዘና (COC) ውጤትን ለማሻሻል የሚያስችል የጋራ የውይይት መድረክ አካሄዱ።
 
መድረኩ የ2017 ዓ.ም. የተመራቂ ሰልጣኞችን የብሔራዊ ምዘና አፈጻጸም ሪፖርት ለመገምገምና የ2018 ዓ.ም. የምዘና ሂደትን በተሻለ ውጤት ለማስፈጸም ያለመ ነው።
 
በዚሁ የውይይት መድረክ ላይ በዊንጌት ክላስተር ስር የሚገኙት የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ የደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ እና የኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዋና ዲኖችና እና የስልጠናና አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዲኖች ተሳትፈዋል። በተጨማሪም ከአዲስ ከተማ፣ ከኮልፌ፣ ከአራዳ፣ ከጉለሌ እና ከልደታ ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ የትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የስራ ኃላፊዎች በጋራ መክረዋል።
 
በዕለቱ የውይይት ሰነዱን ያቀረቡት የሰልጠናና አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዲን ቢሮ የስልጠና ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አየለ ብርሃኑ ሲሆኑ በሰነዳቸውም የሰልጣኞችን የመብቃት ምጣኔ እና የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በዝርዝር አቅርበዋል።
 
ብሔራዊ ምዘና የሰልጣኞችን የሙያ ብቃት የሚያረጋግጥ ወሳኝ ሂደት መሆኑ በመድረኩ ላይ የተገለጸ ሲሆን በቀጣይ ሂደቱ የሚሳተፉ ሁሉም አካላት በቅንጅት፣ በኃላፊነትና በተጠያቂነት በመስራት የ2018 ዓ.ም. የምዘና ውጤትን ከፍ ማድረግ እንደሚገባቸው አቅጣጫ ተቀምጧል።
መድረኩ ሲጠናቀቅም ሁሉም ተሳታፊ አካላት በጋራ በመስራት ክፍተቶችን ለመሙላት የ2018 ዓ.ም

.

Copyright © All rights reserved.

Created with