የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ከዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት (ILO) ጋር በመተባበር በስደት ተመላሾች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።
🇪🇹አዲስ አበባ | የካቲት 28/2018 ዓ.ም🇪🇹
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ስምሪት አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት (ILO) ጋር በመተባበር ለባለድርሻ አካላትና ለዘርፉ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
የቢሮው የሥራ ስምሪት አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ሳብሀዲን ሱልጣን ስልጠናውን በንግግር ሲከፍቱ እንደገለጹት፤ መንግስት ለሥራ ፈላጊ ዜጎች በአገር ውስጥ የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ሰፊ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል። ይሁን እንጂ በተለያዩ ምክንያቶች ከአገር ወጥተው በስደት ላይ የቆዩና ወደ አገራቸው የተመለሱ ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መሥራት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።
የሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል የተያዘው ትኩረት፦በአሁኑ ወቅት የሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን መከላከል በከተማ ደረጃ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት በምክትል ከንቲባ የሚመራ ምክር ቤት ተቋቁሞለት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል። ዜጎች በሕጋዊ መንገድ መጓዝ እየቻሉ ራሳቸውን ለሕገ-ወጥ ደላሎች አሳልፈው በመስጠት በየብስና በባሕር ለሚገጥማቸው መከራና እንግልት መፍትሄ ለመስጠት ቢሮው በትኩረት እየሰራ መሆኑን ዳይሬክተሩ አስረድተዋል።

ይህንን ሀገራዊ ተልዕኮ ለማሳካት በፍትህ ቢሮ አስተባባሪነት በተቋቋሙት ስድስት የሥራ ቡድኖች ውስጥ የሥራና ክህሎት ቢሮ ሁለት ዋና ዋና ተግባራትን በኃላፊነት እየተገበረ ይገኛል። እነሱም፦
የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራት፦ ዜጎች ስለ ስደት አስከፊነትና ስለ ሕጋዊ አማራጮች በቂ እውቀት እንዲኖራቸው ማድረግ።
የስደት ተመላሾችን መልሶ ማቋቋም፦ ተመላሾች በዘላቂነት በኢኮኖሚ ራሳቸውን እንዲችሉ የማድረግ ስራ ናቸው።
ለተመላሾች የተመደበ በጀትና የቀጣይ ዕቅዶች
ቢሮው የስደት ተመላሾችን በዘላቂነት ለማቋቋም 60 ሚሊዮን ብር በጀት መድቦ የስልጠናና የገንዘብ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ አቶ ሳብሀዲን ገልጸዋል። በዚህም መነሻነት በየክፍለ ከተማው አንድ አንድ ሺህ (1,000) ወጣቶችን በመጋበዝ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ተከናውነዋል።
በተጨማሪም ከፍትህ ቢሮ ጋር በመተባበር እና በዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት (ILO) ድጋፍ የተገነባውን የዳታ ሴንተር (Data Center) ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ በዘገባው ተመላክቷል። በመጨረሻም ዳይሬክተሩ ለተደረገው የቴክኒክና የፋይናንስ ድጋፍ ለዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት (ILO) ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
.