አርብ:- መጋቢት 4 ቀን 2018 ዓ.ም
በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስኬቶች ላይ ያተኮረው "ዥረቱ" የተሰኘው ትያትር በኮሌጁ ቀረበ!!
በቴክኒክና ሙያ ስልጠና (TVET) ዘርፍ የታዩ ውጤታማነቶችንና በመዲናችን አዲስ አበባ የተመዘገቡ የልማት እምርታዎችን የሚዘክር "ዥረቱ" የተሰኘ ልዩ የቲያትር ድግስ በትናንትናው ዕለት በኮሌጁ መድረክ ለተመልካች ቀርቧል።
በአቆልቋይ ኢንተርቴመንት ተዘጋጅቶ የቀረበው ይህ ትያትር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ አጋዥነትና በከተማ አስተዳደሩ ሙሉ ይሁንታ የተሰናዳ ነው።
የትያትር ስራው በዘርፉ ያለውን ለውጥ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ ለማስጨበጫ በሚረዳ መልኩ በአዝናኝና በአስተማሪ አቀራረብ የተቀመረ መሆኑ ተገልጿል።
ለ45 ደቂቃዎች በመድረክ ላይ የቆየው ይህ ትያትር በታዋቂና አንጋፋ የጥበብ ባለሙያዎች የተሞላ ነበር። በዝግጅቱ ላይ አርቲስት ሽመልስ ለጋስ እና ደራሲና ተዋናይ ካሳዬ ገበየሁን ጨምሮ ሌሎች አንጋፋና ወጣት የመድረክ ፈርጦች ድንቅ ብቃታቸውን አሳይተውበታል።

ትያትሩ በደራሲና ተዋናይ ካሳዬ ገበየሁ ተደርሶና በአርቲስት ተሻለ ወርቁ ተዘጋጅቶ ለዕይታ በቅቷል።
.